Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Thursday, March 21, 2013

የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች በአብዛኛው ነባር አመራሮቻቸው በስራ አስፈጻሚነት ቀጠሉ


ኢሳት ዜና:-የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ሰሞኑን በተከታታይ ባካሄዱዋቸውና በመተካካት ረገድ እምብዛም ለውጥ ያልታየባቸው ጉባዔዎች በአብዛኛው ነባር አመራሩን ይዘው ሲያስቀጥሉ መጠነኛ የሆነ እርምጃም ወስደዋል፡፡ በዚሁ መሰረት ኦህዴድ አቶ አባዱላ ገመዳን፣ ግርማ ብሩን እና ኩማ ደመቅሳን ከስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነት ሲያሰናብት፤ ብአዴን በበኩሉ የፍትህ ሚኒስትር የሆኑትን አቶ ብርሃን ኃይሉን፣ደኢህዴን ደግሞ አቶ ተሾመ ቶጋን አሰናብቷል፡፡
ብአዴን በጤና ችግር መደበኛ ስራቸውን ማከናወን የተሳናቸውና ነባር ታጋይ የሆኑትን አቶ ህላዊ ዮሴፍን፣ኦህዴድ ወ/ሮ አስቴር ማሞን በኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚነት እንዲመረጡ አድርጓል፡፡በተጨማሪም ኦህዴድ የፌዴራል ፖሊስ ኮምሽነሩን አቶ ወርቅነህ ገበየሁን የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ አባል እንዲሆኑ መርጧቸዋል፡፡

የትግራይ ህዝብ ስማ!!

(ርዕሰ አንቀጽ); http://www.goolgule.com, March 21, 2013
mekelle
ሰሞኑን በውዴታም ይሁን በግዴታ በመቀሌ እጅግ ከፍተኛ የሚባል ቁጥር ያላቸው የትግራይ ተወላጆች ሲጨፍሩ፣ ሲዘሉ፣ ከበሮ እየመቱ የባህላቸውን ዘፈንና ውዝዋዜ ሲያወርዱ አይተናል። ምክንያቱ በግልጽ ባይነገርም ሲደበቅ የነበረው የህወሃት ሃብትና ንብረት ውጤት የሆኑ፣ በልዩ የመንግስት ድጋፍ የተከናወኑ ግዙፍ ተቋሞች በጎዳና ለህዝብ ሲቀርቡም ተስተውሏል። ልማቱ መልካም ነው። ደስ ይለናል። ምንም ተቃውሞ የለንም። ግን መልዕክት አለን።

Sunday, March 17, 2013

መኢአድ መንግስት በዘር ማጥፋት ወንጀል እንዲከሰሰ ጠየቀ

መኢአድ
ኢሳት ዜና:-ድርጅቱ  ” በቋንቋ ማንነት ህዝብን መግደል፣ ማፋናቀል እና ማሰር የዘር ማጥፋት ወንጅል ነው” በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ ” ሰሞኑን በቤንሻንሂል ጉሙዝ ክልል በአማራ ተናገሪ ማህበረሰብ ላይ የተከፈተው ማፈናቀል ፣ በጅጅጋ እና በአፋርም የቀጠለ ሲሆን በመላው  አገሪቱ የአማርኛ ተናጋሪ ህዝብ ቤት እንዳይኖረው ፣ የንግድ እንቅስቃሴ ላይ እንዳይሳተፍ በተለያየ ስልት ደሀ ሆኖ እና በጎዳና እንዲበተን የወያኔ ካድሬዎች አዲስ አበባን ጨም     ሮ በሁሉም ትእዛዝ የሰጡ ሲሆን በአዲስ አበባ ከፈረሱ እና እያፈረሱ ካሉ ቤቶች አብዛኞቹ የአማራ ተናጋሪዎች መኖሪያ መሆናቸውን መታዘቡን ” ገልጿል።

በአዲስ አበባ እና በተለያዩ ከተማዎች የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች የባንክ ብድርን ጨምሮ መሬት እንዳያገኙ ከመደረጉም በላይ ከፍተኛ ግብር እየተጫነባቸው በመሆኑ ከንግድ ስርአቱ እንዲወጡ ተድርጓል ብሎአል መኢአድ በአሁኑ ጊዜ ከ200 በላይ ከቤንሻንጉል ጉምዝ የተፈናቀሉ የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች በባህርዳር ያለመጣለያ በጎዳና እየኖሩ መሆኑን መኢአድ በመግለጫው አመልክቷል።በባህርዳር ለጎዳናና ተዳዳሪነት ከተዳረጉት መካከል ብዙ ነፍሰጡሮችና ህጻናት የገኙበታል።

የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ይዞታ: ኢትዮጵያ

ARCHIV - Pakistanische Journalisten protestieren in Karachi gegen die Behinderung ihrer Arbeit (Archivfoto/Illustration vom 16.03.2007). Die Vereinten Nationen begehen auf Initiative ihrer Kulturorganisation UNESCO seit 1994 jährlich am 3. Mai den Tag der Pressefreiheit. Foto: Nadeem Khawer (zu dpa-Themenpaket vom 28.04.) +++(c) dpa - Bildfunk+++
pixel

የኢትዮጵያ መንግሥት በህገ መንግሥቱ የተቀመጡትን መሠረታዊ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች በማስጠበቅና በማስከበር ላይ እንደሚገኝ ይናገራል ። ይሁንና በህገ መንግሥቱ የተደነገጉ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ፣ በሌሎች ህጎች ምክንያት ሊተገበሩ አልቻሉም ሲሉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ስሞታ ያቀርባሉ ።አለም አቀፍ የመብት ተከራካሪ ድርጅቶች የውጭ መንግሥታት የሐገር ውስጥ ተቃዋሚ ፓርቲዎችና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች እንደማይከበሩ በተለያዩ ጊዜያት በሚያወጧቸው ዘገባዎች ይጠቁማሉ ። የኢትዮጵያ መንግሥት ግን እነዚህን ዘገባዎች አይቀበልም ። ይልቁንም በህገ መንግሥቱ የተቀመጡትን መሠረታዊ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች በማስጠበቅና በማስከበር ላይ እንደሚገኝ ይናገራል ። 

የኢህአዴግ አፋኝ አስተዳደር የአፓርታይድ ቅርጽ እየያዘ ነው!

የኢህአዴግ አፋኝ አስተዳደር የአፓርታይድ ቅርጽ እየያዘ ነው!ሰማያዊ ፓርቲ
ዛሬ መጋቢት ስምንት ቀን 2005 ዓ.ም ከጠዋቱ 3 ሰዓት ለኢትዮጵያ ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽነት ማህበር፤ ሰማያዊ ፓርቲ እና ባለራዕ ወጣቶች ማህበር በጋራ በመሆን “ለፋሽስቱ የጦር ወንጀለኛ ለማርሻል ግራዚያኒ ክብር መስጠት የአባቶቻችን መስዋዕትነት ማራከስ ነው” በሚል የተጠራውን ሰልፍ አምባገኑ የኢህአዴግ መንግስት በርካታ የፌደራል ፖሊስ፣ የደህንነት አባላትን እና የአዲስ አበባ ፖሊሶችን በማሰማራት ሲበትን፤ የተቋማቱን ከፍተኛ አመራሮች፤ ታዋቂ ግለሰቦች እና በርካታ ወጣቶች ጨምሮ ቢያንስ 34 ሰዎች አስሯል የታሳሪዎች ቁጥር አሁንም በመጨመር ላይ ነው፡፡

እንዲሁም በትላንትናው እለት ለተቃውሞ ሰልፉ የቅስቀሳ ስራ ሲሰሩ ከነበሩት ውስጥ 2 የሰማያዊ ፓርቲ የስራ አስፈጻሚ አባላትን እንዲሁም የባለራዕይ ወጣቶች የስራ አስፈጻሚ አባላትን ጨምሮ 8 ሰዎችን አስረዋል፡፡

ኢትዮጵያዊቷ በሶርያ ያሳለፈችውን ስቃይ *የወንድ ልጅ ብልት ቆርጠው “ተጫወችበት” ይላሉ

ኢትዮጵያዊቷ በሶርያ ያሳለፈችውን ስቃይ *የወንድ ልጅ ብልት ቆርጠው “ተጫወችበት” ይላሉ*የወንድ ልጅ ብልት ቆርጠው “ተጫወችበት” ይላሉ— *ቦንብ ታጥቀሽ ራስሽን አፈንጂ ተብዬ ነበር —- *አፍሪካውያንን በኤሌክትሪክ ማቃጠል የተሰጠኝ የሥራ ኃላፊነት ነበር— *ውሃ ስንጠይቅ ሽንታቸውን ነበር የሚሰጡን …እላያችን ላይ ይሸናሉ … ከአማርኛ ይልቅ አረብኛ መናገር ይቀናታል፡፡ የምትናገረው በቁጭት፣ በእልህና በፍርሃት ስሜት ነው፡፡

 ከአራት ዓመት በፊት ለሥራ ወደ ሶሪያ የተጓዘችው ሃረግ (ሜሪ)፤ በሶርያ ከጦርነቱ መጀመር ጋር ተያይዞ ያሳለፈችውን መከራና ስቃይ በአንደበቷ ትናገራለች – አንዳንዴ በሰመመን፣ ሌላ ጊዜ በመንገሽገሽ፡፡ ከሶሪያ በሱዳን በኩል አድርጋ ወደ ኢትዮጵያ በገባች በአምስተኛ ቀኗ ከጋዜጠኛ አበባየሁ ገበያው ጋር ያደረገችውን ቃለምልልስ ከዚህ በታች አቅርበነዋል፡፡ በሶርያ በምን ሥራ ላይ ነበር የተሰማራሽው? በ2009 ዓ.ም ወደ ሶርያ የሄድኩት በአውሮፕላን ነበር፡፡ እንደሌሎች ሴት እህቶቼ የቤት ውስጥ ሥራ ሳይሆን እርሻ ላይ ነበር ሥራ ያገኘሁት፡፡ ሥራዬ የወይራ ፍሬ መልቀም እንዲሁም ሙዝ፣ ትፋህ፣ አትክልትና ፍራፍሬ መኮትኮት፣ ማጨድ፣ ወዘተ ነበር፡፡ 

ሰበር ወሬ… ጣሊያንን የተቃወሙ ኢትዮጵያውያን በገዛ መንግስታቸው ታሰሩ!

ነገሩን ድንገት ስለሰማነው ሰበር እንበለው እንጂ ወሬው እነኳ ቅስም የሚሰብር ነው፡፡ ዛሬ መጋቢት 8 2005 ዓ.ም በርካታ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያኖች ጣሊያን ለጨፍጫፊው ግራዚያኔ ያሰራችውን ሀውልት ለመቃወም ከስድስኪሎ አደባይ እስከ ጣሊያን ኤንባሲ የመ፣ዘልቅ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ተሰባስበው ነበር፡፡

ሰላማዊ ሰልፉ ገና ከመጀመሩ የደረሱት ፖሊሶች እጃቸው የገባውን ሀገር ወዳድ በሙሉ አስረው ወሰዱ፡፡ ከዛም በፖሊስ ጣቢያዎች ባሉ እስር ቤቶች ጨመራቸው፡፡