Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Saturday, October 6, 2012

የ21ኛው ክፍለ ዘመን ይሁዲ: ከማተቤ መለሰ ተሰማ

በ20ኛው ክፍለ ዘመን የአርያንን ዘር በዓለም ላይ ማንገስን ሰነቆ የተነሳው የጀርመኑ ናዚ፡ በይሁዲያዊያን ላይ የፈጸመው የዘር ማጥፋት ሰቆቃ ዛሪ ድረስ የዓለምን ህዝብ ሲያሳዝን ይገኛል። አሁን በ21ኛው ክፍለዘመን ደግሞ ወያኔ የአማረኛ ቋንቋ ተናጋሪና የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታይ የሆነውን ኢትዮጵያውያን ከምድረገጽ ለማስወገድ እንደ ያኔው ናዚ ዘግናኝ ድርጊት በመፈጸም ላይ ነው።

ይህ የጥፋት ዘመቻ በአጋጣሚ የተከሰተ ሳይሆን በእቅድ ተነድፎ እየተከናወነ ያለ መሆኑን የህዋሀቱ አንጋፋ ታጋይ አቶ ስብሃት ነጋ የአቶ ሐይለማርያም ደሳለኝን የኢስሙላ ጠቅላይ ሚኒስተርነት ሹመት አስመልክቶ ገዛ ተጋሩ ከተባለ ፓለቶክ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ፡ ስልጣንን ከኦርቶዶክስ እምነት ተከታይና ከአማራ ነጥቀነዋል አላማችንም የኸው ነበር ሲሉ ሰነምግባር ባልገራው አንደበታቸው በድፍረት መናገራቸው የወያኔ ጉዞ ከየት ወዴትነት ማሳየት ከሚችሉ ኩነቶች እንደ አንዱ ሊወሰድ የሚገባው ነው።

Thursday, October 4, 2012

በሰሜን ሸዋ የሚገኙ መምህራን በፖለቲካ አቋማቸው ምክንያት እየታደኑ ነው

መስከረም ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የሰሜን ሸዋ መምህራን ለኢሳት እንደገለጡት፣ የኢህአዴግ መንግስት አንድ ለአምስት በሚለው አደረጃጀቱ የግንባሩ አባላት ለመሆን ፈቃደኛ አልሆኑም ያላቸውን መምህራን እያዋከበ ነው።

የኢህአዴግ አባል ለመሆን ፈቃደኛ አልሆኑም የተባሉ መምህራን የአመለካከት ችግር አለባቸው፣ ከሌሎች የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት አባላት ጋር  ትሰራላችሁ፣ የራሳችሁን የፖለቲካ አመለካከት ታራምዳላችሁ እየተባሉ ወከባና ማስፋራሪያ ሲደርስባቸው መቆየቱን መምህራን ይናገራሉ።

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ ለሀይለማርያም ማሞ ከፍተኛ ትምህርት መሰናዶ በቁጥር ሰ/ሸ/ዞ/ፖ/መ/1012/04 በቀን 28/10/2004 ዓም በጻፈው ደብዳቤ ላይ  ብርሃኔ አሰብአለሁ ደረሰ፣  ባይሌ ደርሰህ ምህረቴ እና  አሰፋ ወንድሙ መከተ የተባሉት መምህራን በትምህርት ቤቱ ውስጥ የራሳቸውን የፖለቲካ አመለካከት ሲያራምዱ በመገኘታቸው እየታደኑ መሆኑን ገልጿል።

Tuesday, October 2, 2012

ኢህአዴግ የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ እና የጋዜጣው ከፍተኛ አዘጋጆችን ለማሰር መሰናዶ እያደረገ መሆኑን ምንጮቻችን ገለጹ

Temesgen Desalegn and his main editors
ኢሳት ዜና:-የደህንነት ሰዎችም በድጋሚ የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ውሎና አዳር መከታተል መጀመራቸውን ለጋዜጠኛው ቅርበት ያላቸው የዓይን እማኞች ገልጸውልናል፡፡ ጋዜጠኛ ተመስገን እንደገለጠው በዛሬው እለት የደህንነት ሰዎች በአካባቢው ባይታዩም እስካለፈው ቅዳሜ ድረስ ማንነታቸው የማይታወቁ ሰዎች ሲከታተሉት እንደነበር ገልጧል። የኢሳት ዘጋቢ ከጋዜጠኛ ተመስገን ጋር ቃለምልልስ በሚያደርግበት ወቅት ስልኩ በተደጋጋሚ እየተቋረጠ ሲቸገር መዋሉን  ገልጧል።

የሳዑዲ መንግስት በሐጂና ዑምራ ኢትዮጵያዊያን ተጓዦች ላይ ጥሎት የነበረውን እገዳ አነሳ

ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ የሳዑዲ ኤምባሲ ምንጮች አንዳንድ ሁኔታዎችን ለማጣራት ለተወሰኑ ቀናት ቪዛ መስጠት ከማቆም ውጪ እገዳ አልነበረም ሲሉ መንግስታቸው ጥሎአል የተባለውን እገዳ አስተባብለዋል፡፡ ለኢትዮጵያ እስልምና ም/ቤት ቅርበት ያላቸው ምንጮች ግን እገዳው ለተወሰኑ ቀናት ተጥሎ ከቆየ በኃላ በጉዳዩ የኢትዮጵያ መንግስት ጣልቃ ገብቶ በተደረገ ውይይት ቪዛ የመስጠቱ ሥራ መቀጠሉን ተናግረዋል፡፡

ሽማግሌ ሲሸብት ይጨምታል ፣ የእንጨት ሽበትስ? እንግዳ ታደሰ

Ato Sebhat Nega
የአቦይ ስብሃትን አማራና ኦርቶዶክስ  የሚል ያልተሞረደ  አነጋገር  በገዛ ተጋሩ ላይ ሳደምጥ ፣እንደ ወራጅ ዉሃ አሳዳሪ ማጣት እያለች የምትዘፍን  አቀንቃኝ  ዜማ ትዝ አለኝ ፡፡ ሽበታቸው ዉብታቸው ሳይሆን ፣ ሽበታቸው ነውራቸው የሆነባቸውን የንጨት ሽበቶችን በማምሻ እድሜያቸው ላይ ስትመለከቱ ምን ይሰማችኋል ? ባህላዊ እሴቶቻችንና – ሃይማኖታችን በጸያፍ እንዳንናገር የሚያግዱንን ያልተሞረዱ አነጋገሮች እንዳመጣላቸው የሚናገሩ፣ ቂመኛ እና የድፍ ማስወገጃ ቦይ የሆኑትን ፣ በአንድ ዘር ላይ ያነጣጠረ ያደፈ አነጋገርን ፣ ከውሃት አመሰራረት ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ሳይለወጡ የሚናገሩትን የአቦይን አነጋገር ስትሰሙ   ምን ተሰማችሁ ? የአቦይ መንግሥት በቻይናዎች የሚደገፍ መንግሥት በመሆኑ ፣ ምናልባት ከቻይናዎች ጥቅስ ብንጠቅስላቸው ቶሎ ሊረዱት ስለሚችሉ እነሆ ጥቅሱ ፡፡

Sunday, September 30, 2012

ዊኪሊክስ በኢትዮጵያ አውሮፕላን ላይ ተፈጽሟል የተባለውን ሴራ አጋለጠ

በዓለም እጅግ አነጋጋሪና ገናና ለመሆን የበቃው የዊኪሊክስ ድረ ገጽ ይፋ ባወጣው አዲስ መረጃ የበረራ ቁጥር “ET-409” የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 አውሮፕላን፣ ከቤይሩት ራፊቅ ሐሪሪ አውሮፕላን ማረፊያ ጥር 17 ቀን 2002 ዓ.ም. ከመነሳቱ ወዲያው ሲከሰከስ፣ የእስራኤል የስለላ ድርጅት ሞሳድ በተሳተፈበት ምስጢራዊ የደኅንነት ሥራ ሳቢያ ሰለባ ሳይሆን እንዳልቀረ አመለከተ፡፡