Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Saturday, September 29, 2012

በመተማ ከአቶ መለስ ሞት ጋር በተያያዘ ከ120 በላይ ሰዎች ታሰሩ

ኢሳት ዜና:-ኢሳት እንዳረጋገጠው በአማራ ክልል በሰሜን ጎንደር ዞን በመተማ ከተማ በአቶ መለስ ዜናዊ ሞት ደስታችሁን ገልጣችሁዋል የተባሉ ከ120 በላይ ሰዎች ታስረው ስቃይ እየደረሰባቸው ነው።

የመተማ አካባቢ ነዋሪዎች   እንደገለጡት አቶ መለስ ዜናዊ ሞታቸው እንደተሰማ ” መለስ እንኳንም ሞተ፣ ተገላገልን” በማለት በመጠጥ ቤቶች ውስጥም ሆነ በተለያዩ ቦታዎች ደስታቸውን ገልጠዋል የተባሉ ከ120 በላይ ሰዎች ታስረዋል።

የወደፊቱ፡ የዓለም ስጋትና የሀገራችን ሁኔታ፡(ማተቤ መለሰ ተሰማ)

Matebe Melese

የሰውን ልጅ ታሪክ ወደኋላ መለሥ ብለን ሥንመረምር፡ ከፍጡራን ሁሉ በተሻለ ሁኔታ ዓለምንና ተፈጥሮን አጣጥሞ በመግራት እየተጠቀመባት እንዳለ ለመረዳት አያዳግተንም፡፡ በዚያው ልክ ደግሞ አንዱ ሌላውን የበታች አድርጎ ለመግዛትና ለመበዝበዝ ሌላው ላለ መገዛትና ላለመበዝበዝ በሚደረጉ ፍልሚያዎች መነሻ ነት ለጥፋትም እያዘጋጃት መሆኑን እናያለን፡፡ በእነዚህ ትንቅንቆች ሂደት መጠነ ሰፊ የህይወትና የንብረት ውድመቶች የደረሱና እየደረሱም ያሉ ወደፊትም በዳይና ተበዳይ በዝባዢና ተበዝባዥ በአንድ ቃል አምባ ገነኖች፡ ከምድራችን እስካለተወገዱ ደረስ እንደማያቆሙ የታወቀ ነው።

‹‹ተቃዋሚ ፓርቲዎች በመሰባሰብ ትልቅ ጉልበት መፍጠር አለባቸው›› (አንዱዓለም አራጌ)

Andualem Aragie

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) ከፍተኛ አመራሮች መስከረም 17 ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም በሽብርተኝነት ስም ታስሮ የሚገኘውንና እና የፓርቲው ከፍተኛ አመራር የሆነውን አቶ አንዱዓለም አራጌን ቃሊቲ በመገኘት ከብዙ ጭቅጭቅ በኋላ በአካል በመገኘትና ለመጠየት በቅቷል፡፡ አመራሩ በተጨማሪም የአንድነት ፓርቲ የብሔራዊ ም/ቤት አባል የሆነውንና ቂሊንጦ ታስሮ የሚኘውን አቶ ናትናኤል መኮንንም እንደጠየቀ የህዝብ ግንኙነት ክፍል ገልጿል፡፡

Friday, September 28, 2012

በደቡብ ክልል የተለያዩ ከተሞች ነዋሪዎች <በአቶ ሀይለማርያም ሹመት ለውጥ ይመጣል ብለን አናስብም> ሲሉ ተናገሩ

ኢሳት ዜና:-አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ከደቡብ ክልል ከወላይታ ብሄረሰብ የተገኙ መሆናቸው በክልሉ ነዋሪዎች ዘንድ ምን ስሜት ፈጠረ የሚለውን ለማወቅ ኢሳት ከተለያዩ የክልሉ ነዋሪዎች ጋር  ቃለምልልስ አድርጓል።

በደቡብ ክልል ” መለስ ዜናዊ እንኳን ሞተ” ብለው ተናግረዋል የተባሉ 80 ሰዎች ታሰሩ

ኢሳት ዜና:-በደቡብ ኦሞ ዞን በደቡብ አሪ ወረዳ የሚገኙ አርሶአደሮች፣ ” መለስ ዜናዊ እንኳንም ሞተ፣ አናዝንም” በማለት ሲናገሩ ተሰምተዋል በሚል ነው የወረዳው አቃቢ ህግ ክስ ያቀረበባቸው። የክስ መዝገቡ እንደሚያመለክተው አርሶ አደሮቹ በኢፌዲሪ ወንጀል ህግ አንቀጽ 4 /86 ሀ ላይ የተደነገገውን ተላልፈዋ ል። 

Tuesday, September 25, 2012

አቶ በረከት የኢቲቪና የፕሬስ ድርጅት ሥራ አስኪያጆችን አንስተው ታዛዦቻቸውን ሊሾሙ ነው ተባለ

ኢሳት ዜና:-የኮሙኒኬሽን ሚኒስትሩ አቶ በረከት ስምዖን  የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እና የኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ሥራ አስኪያጆችን በማንሳት ለእርሳቸው ታዛዥ የሆኑ ሰዎችን ለማስቀመጥ  እንቅስቃሴ መጀመራቸው ተጠቆመ።

በዚህም መሰረት ከደቡብ ክልል ያስመጡትና በኢትዮጵያ ራዲዮ ውስጥ በምክትል ሥራ አስኪያጅነት ሢሰራ የቆየው ሰለሞን ተስፋዬ የኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣የ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ምክትል ዋና አዘጋጅ ሰይፈ ደርቤ ደግሞ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት  ዋና ሥራ አስኪያጅ እንዲሆኑ ወስነው ይህንኑ ተግባራዊ ለማድረግ እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን ምንጮቹ ገልጸዋል።

ዶላር አዘዋዋሪዎቹ ደላሎች!!

Source: (http://www.goolgule.com/) ህወሓት የአጋር ፓርቲዎቹን የንግድ ተቋማትና ልማታዊ ባለሀብት እያለ የሚጠራቸውን አባላቱን በዋናነት አሰባስቦ ያቋቋመው የወጋገን ባንክ ውለታ ባስገባቸው የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች አማካይነት በቀን እስከ ሁለት ሚሊዮን የሚጠጋ ዶላር የመሰብሰብ አቅም መገንባቱ ተጠቆመ።

የጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የአዲስ አበባ ዘጋቢ ባካሄደው ማጣራት ወጋገን ባንክ ከፖለቲካው አመራር ባለው ቀጥተኛ ድጋፍና ሽፋን በመታገዝ ወደ ኢትዮጵያ የሚተላለፈውን የውጪ ምንዛሪ መቆጣጠር ያስቻለውን አቅም የገነባው በአስገዳጅ ደንብ ነው። በሶማሌ ተወላጆችና በህወሓት ሰዎች አማካይነት በሽሪክነትና በተናጥል የተቋቋሙ የገንዘብ አዘዋዋሪ ተቋማት ስራውን መስራት የሚያስችላቸውን ፈቃድ ሲያወጡ ከወጋገን ባንክ ጋር ብቻ ለመስራት አስቀድመው ውል እንደሚፈጽሙ ያስታወቀው ዘጋቢያችን፤ በዚሁ መሰረት ውል ከገቡት የገንዘብ አሰባሳቢ ድርጅቶች መካከል ዋንኞቹን በስም ዘርዝሯል።

ቀይ መብራት --የሃይለማርያም ደሳለኝን እና የደመቀ መኮንን የተደበቀ ታሪክ


  • ·        አንደኛ ……….. ጠቅላይ ሚኒስትር …….   ONLY JESUS (የሐዋርያ እምነት ተከታይ)
  • ·        ሁለተኛ ……….ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ….. MUSLIM
  • ·        ሶስተኛው …. ጠቅላይ ሚኒስር ለመሆን የታጩት ሰው ….. MUSLIM

Monday, September 24, 2012

Dr. Berhanu Nega: What is the “ecstatic hope” behind Hailemariam’s new leadership?


የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ የነበሩት ኮበለሉ

ኢሳት ዜና:- በአሁኑ ወቅት በኃላፊነት ላይ ባለው የኩማ አስተዳደር የአዲስአበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና የማስታወቂያ ቢሮ ኃላፊ በመሆን ያገለገሉትና ከአንድ ዓመት በፊት በአቅም ማነስ ተተችተው ከኃላፊነታቸው የተነሱት አቶ ከፍያለው አዘዘ ወደ ዩናይትድስቴትስ አሜሪካ ቤተሰባቸውን ይዘው መኮብለላቸው ተሰማ፡፡

አቶ ከፍያለው ከ1997 ዓ.ም ምርጫ አለመግባባት ጋር በተያያዘ በገዥው ፓርቲ ተሹሞ የነበረውን የባለአደራውን የአቶ ብርሃነ ደሬሳ አስተዳደር በግንቦት ወር 2000 ዓ.ም በይስሙላ ምርጫ በተካው የአቶ ኩማ ደመቅሳ ካቢኔ ውስጥ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የሥራአስኪያጅነት ኃላፊነታቸው በመነሳት በቀጥታ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ ለመሾም ችለው  ነበር፡፡
ኢሳት ዜና:-የህወሀት መስራች የሆኑት አቶ ስብሀት ነጋ ይህን ያሉት ሰሞኑን ለንባብ ከበቃው አዲስ ጉዳይ መጽሔት ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ነው።

ቀደም ሲል  የህዝባዊ ወያነ ሀርነት ትግራይ-ህወሀት ሊቀ-መንበር ሆነው የተመረጡት አቶ አባይ ወልዱ ብሔራዊ እርቅ  የሚለው ጥያቄ  ፈጽሞ ተቀባይነት እንደማይኖረውና  ጥያቄውን የሚያነሱ ሀይሎችን  እንደሚታገሏቸው  መናገራቸው ያታወሳል።

በኮሪያ የኢትዮጵያ ኢምባሲ የባጀት ጥረት ገጠመው

ኢሳት ዜና:-በደቡብ ኮሪያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ በበጀት ዕጥረት ምክንያት እኤአ 2001  በሩን ዘግቶ ከተመለሰ በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ በ2012  ቢከፈትም ገና ስራውን ከጀመረ 3 ወራትን ሳያስቆጥር ዳግመኛ የበጀት እጥረት እንደገጠመውና ለሰራተኞቹ የሚከፍለው ደመወዝ እንዳጣ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የውስጥ ሰራተኛ አስታወቁ።

በተባበሩት ዓረብ ኢምሬት በሻርጃህ ከተማ 36 ኢትዮጵያውያን ሴቶች ታሰሩ

ኢሳት ዜና:- ኢምሬት ኒውስ እንደዘገበው ኢትዮጵያውያኑ በሻርጃህ ፖሊስ የታሠሩት ከስፖንሰሮቻቸው ጠፍተው በመገኘታቸው ነው።

ኢትዮጵያውያኑ  በኢምሬት -አረብ ቪላ ውስጥ እንደሚገኙ መረጃ ከደረሰው በሁዋላ በቁጥጥር ሥር  እንዳዋላቸው የገለጸው የሻርጃህ ፖሊስ፤ በህገ-ወጥ መንገድ በሥራ ተሰማርተው እንደነበር አመልክቷል።

ሰለጠቅላይ ሚንስቴር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ፦ ያልተባሉና ያልተነገሩ: by Zone9


ይህ ጦማር  በኢትዮጵያ እንዳይነበብ በታገደው በዞን ዘጠኝ ጦማር.  ላይ ይገኛል::
በቀድሞ ተማሪያቸው
I.      መግቢያ፡-

የጠቅላይ ሚንስተር አቶ መለስ ዜናዊ ድንገተኛ ሞት ተከትሎ የአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ያልተጠበቀና ያልታሰበ ወደስልጣን መምጣት ብዙዎችን ያስገረመ ጉዳይ ሲሆን ይህንንም ተከትሎ የዚች ሃገር  ጉዳይ  ያገባኛል ያሉ ብዙ ግለሰቦች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማሀበራት እና ሌሎችም የሳቸው ሹመት ለሃገሪቱ ጥሩ አጋጣሚ ሊሆን እንደሚችልና ምናልባትም ፈጣሪ ለዚች ሃገር ለውጥ ያስቀመጣቸው ሊሆኑ ሁሉ እንደሚችሉ ተስፋ አድርገውባቸዋል፡፡ እኔም ከነዚህ ወገኖች አንዱ ነኝ፡፡

 ስለ ጠቅላይ ሚንስተር ኃይለማርያም ደሳለኝ በተለያዩ ድህረገጾችና ጋዜጦች ብዙ የተባሉና የተጻፉ ሲሆን አብዛኞቹ የሳቸውን በጎና ጥሩ ጎኖች የሚዳሰሱ ናቸው፡፡ ከዚህም መካከል ሰውየውን ጥሩ ሃይማኖተኛና፣ ፈርሀ እግዚአብሔር ያላቸው፣ የመልካም ስነምግባር ባለቤት፣ ቅንና ተንኮል የሌለባቸው፣ ጥሩ አስተማሪና አስተዳዳሪ የነበሩ፣ ቤተሰባቸውን የሚወዱና የሚያከብሩ፣ ሰውን የማይጎዱ፣ ምንም አይነት ሱስ የሌለባቸውና ሙስናን የሚጸየፉ ወዘተ… የሚሉ ናቸው፡፡ እኔም ከሞላ ጎደል በነዚህ የሰውየው ባህሪያቶች እና ገለጻዎች እስማማለሁ፡፡

Sunday, September 23, 2012

የበረከት-አዜብና የስብሃት ፍጥጫ (ከእየሩሳሌም አርአያ)

በሽማግሌው ስብሀት ነጋና በረከት ስምኦን መካከል ስር ሰዶ የቆየው የውስጥ ሽኩቻ እየከረረ ሔዶአል ።አዜብ መስፍን ከበረከት ጎንተሰልፈዋል። አዜብ ለፓርቲው ሊቀምንበርነት «ይመጥናሉ» ያሉዋቸውንና «መለስን ይተካሉ» ሲሉ በድፍረት የተሟገቱላቸው ሁለት አመራር አባላት ተቀባይነት አለማግኘታቸው አበስጭቶአቸዋል አዜብ የጠ/ሚ/ር እንዲሆኑ የተሟገቱላቸው  ቴዎድሮስ አድሀኖም ከእጩነት ራሳቸውን በማግለል ኩም አድርገዋቸዋል።

ከኢትዮጵያ ተስፋ ወጣቶች ድርጅት የተሰጠ መግለጫ

አገራችን ኢትዮጵያ በየዘመኑ ተነስተው የወደቁ የአገዛዝ ስርአቶች አስተናግዳለች፤ሁሉም አገዛዞች በዘመናቸው ህዝቡን በተለያየ መልኩ ገዝተዋል። ህዝባችንም ላልተስማሙት ገዢዎቹ በየወቅቱ ተነስቶ አስፈላጊውን አመጽ በማካሄድ ለውጥ አምጥቷል ። 

ዛሬ በ፳፩ኛው ክፍለ ዘመን አለም በዲሞክራሲ እና በሰብአዊነት የተሻለ ደረጃ በደረሰበት ግዜ አገራችን ኢትዮጵያን እየገዙ ያሉት የባንዳውና ዘረኛ አንባገነን ወያኔ ገዢዎች እና ጭፍራዎቻቸው ህዝባችንን ከመቼውም ግዜ በላይ በከፋ መልኩ በጭካኔ እየገዙት ይገኛሉ።

ሕወሓት የትጥቅ ታጋዮቹን ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር አድረጎ መረጠ

Reporter: በዘካሪያስ ስንታየሁ
በትጥቅ ትግሉ ወቅት ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት)ን ለበርካታ ዓመታት፣ እንዲሁም ከድል በኋላ ድርጅቱን ለ21 ዓመታት የመሩት የአቶ መለስ ዜናዊን ሕልፈተ ሕይወት ተከትሎ፣ ድርጅቱ የትጥቅ ተጋዮቹን ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ ሾመ፡፡

የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አባይ ወልዱ የሕወሓት ሊቀመንበር ሲሆኑ፣ የኮሙዩኒኬሽንና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ደብረፅዮን ገብረ ሚካኤል ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል፡፡

ወጣቱ በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ሞት ምክንያት ከ10ኛ ፎቅ ተከስክሶ ሕይወቱ አለፈ

በታምሩ ጽጌ
የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሕልፈተ ሕይወትን ከሰማበት ዕለት ጀምሮ መሪር ሐዘን ውስጥ ገብቶ የነበረው ወንድወሰን ተስፋዬ የተባለ የ30 ዓመት ወጣት ከአሥረኛ ፎቅ ላይ ተከስክሶ ሕይወቱ ማለፉ ታወቀ፡፡