Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Friday, September 14, 2012

“መለስ የቆፈሩት ጉድጓድ…”

ጎልጉል የድረ-ገጽ ጋዜጣ
ይህንን ቃለምልልስ ያደረግነው ለበርካታ ዓመታት ለኢህአዴግ ሲሰራ ከነበረና በአሁኑ ወቅት ለከፍተኛ ትምህርት ውጪ አገር ከሚገኝ ኢትዮጵያዊ ጋር ነው፡፡ ለደኅንነት ሲባል ስሙን ከመጥቀስ ተቆጥበናል፡፡

ጎልጉል ፦ የጠ/ሚኒስትር መለስ መታመም ድንገተኛ ነው የሚሉ አሉ፤ አሟሟታቸውም ድንገት ነው የሚሉ አሉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ አጋጣሚው መልካም እንደሆነ የሚጠቁሙ አሉ አንተ ከየትኛው ወገን ነህ?

Thursday, September 13, 2012

ESAT New year Message Dr Birhanu Nega

Dr. Berhanu Nega was elected as mayor of Addis Ababa, Ethiopia in the Ethiopian general elections, 2005. He is a founding chairman of the Rainbow Ethiopia: Movement for Democracy and Social Justice and a Deputy Chairman of Coalition for Unity and Democracy (CUD), for whom he served as chief election campaign strategist. Dr. Berhanu is also the co-founder of Ginbot 7 Movement for Justice, Freedom and Democracy, an opposition party and he is currently a chairman of the party.  see the video Speech.

አና ጎሜዝ መለስ የሞቱት በሃምሌ መሆኑን አጋለጡ

(Sept. 12) የአውሮጳ ፓርላማ አባል የሆኑት አና ጎሜዝ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ምንም እንኳን የሞቱት በሃምሌ (July) ወር መሆኑን አጋልጠው አንባገኑ የኢትዮጵያ መንግስት በሚስጥር ይዞ ጭቆናውን ለመቀጠል ሲሞክር እና ይፋዊ የስልጣን ሽግግር አለማድረጉን የአውሮፓ ፓርላማ በቸልታ መመልከቱ አግባብ አለሞሆኑን በቅርቡ በፓርላማው ስብሰባ ላይ ተናገሩ።

በኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ጨቋኝ አገዛዝ እንዲቀጥል የማድረግ ሙከራ ለማስተካከል አለመጣሩ፤ ከአውሮፓ ሕብረት የጋራ የውጭና የደህንነት ስትራቴጂክ ጥቅም ጋር ይጋጫል ሲሉ ተናገሩ።

የተሰጠው ወታደራዊ ሹመት በመከላከያ ውስጥ ያለውን ቅሬታ ተጠቆመ

ኢሳት ዜና:- በምክትል ጠ/ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ አቅራቢነት ማክሰኞ ዕለት የተሰጠው ወታደራዊ ሹመት ከብሔራዊ ተዋጽኦ አንጻር በመከላከያ ውስጥ ያለውን የቆየ ቅሬታ ማባባሱን ምንጮች ጠቆሙ፡፡

ትላንት ከሕመማቸው በማገገም ላይ ባሉት ፕሬዚዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ የተሰጠው ወታደራዊ ሹመት 34 የመከላከያ ኮሎኔሎችን ወደ ብርጋዴር ጄኔራል ያሳደገ ሲሆን ከነዚህ ሹማምንት መካከል ከግማሸ በላይ የሚሆኑት የቀድሞ የህወሃት ታጋዮች መሆናቸው ከብሔር ተዋጽኦ አንጻር ወትሮም የነበረውን ውጥረት እንዳባባሰው ምንጫችን ጠቁመዋል፡፡

አቶ አባይ ወልዱ አቶ መለስ ዜናዊን በመተካት ሊቀመንበር ሆኑ::

ኢሳት ዜና:- የህወሃት ሥራ አስፈጻሚ ሰሞኑን ባካሄደው ስብሰባ በሟቹ በአቶ መለስ ምትክ በአሁኑ ወቅት የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት የሆኑትንና የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር የነበሩትን አቶ አባይ ወልዱን ሊቀመንበር አድርጎ ሲመርጥ ኦህዴድ በበኩሉ ከህመም ጋር በተያያዘ የመልቀቂያ ደብዳቤ ባስገቡት አቶ አለማየሁ አቶምሳ ምትክ የአ/አ ከተማ ከንቲባ የሆኑትን አቶ ኩማ ደመቅሳን መምረጡን ምንጫችን ጠቁሟል፡፡

አዲሱ አመራር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝን ጠ/ሚኒስትር፣አቶ ኩማ ደመቅሳን ምክትል በማድረግ ከስድስትወር በኃላ እስከሚካሄደው የግንባሩ ጉባዔ ድረስ እንዲያገለግሉ በቅርቡ ይሾማቸዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በሊቢያ የአሜሪካ አምባሳደር ተገደሉ።

ኢሳት ዜና:- በሊቢያ ምሥራቃዊ ግዛት በቤንጋዚ በሚገኘው የ ዩናይትድ ስቴትስ ቆንስላ ታጣቂ ሚሊሺያዎች ድንገት በከፈቱት ጥቃት  በአሜሪካ የሊቢያ አምባሳደርን ጨምሮ አራት የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት ተገደሉ።

ቢቢሲ እንደዘገበው፤ታጣቂዎቹ፤አምባሳደር ክርስቶፈር ስቴቨንስ እና ሦስት ሌሎች የዩናይትድስቴትስ ባለስልጣናትን የገደሉት፤ አሜሪካ ውስጥ በተዘጋጀና የነቢዩ መሀመድን ታሪክ ያጎደፈ ነው ባሉት ፊልም ምክንያት ተተቃውሟቸውን ለመግለጽ ነው።

Tuesday, September 11, 2012

ሀገሪቱን አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትርና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጋራ ይመሯታል ተባለ

ኢሳት ዜና:-በመስከረም ወር 2005 ዓ.ም የኢህአዴግ ምክር ቤት በአቶ መለስ ዜናዊ ምትክ በሚያካሂደው ምርጫ የሚመረጠው ሊቀመንበር እና ምክትል ሊቀመንበር ድርጅቱን ለስድስት ወራት ብቻ በጋራ እንደሚመሩ አቶ ሬድዋን ሁሴን የግንባሩ ጽ/ቤት ኃላፊ አስታወቁ፡፡

አሜሪካ የተደበቀው ወንጀለኛ (ከእዮሩሳሌም አርአያ)

የህወሃት አባል ነው ። ከትጥቅ ትግሉ ዘመን አንስቶ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ስልጣን እስከተቆናጠጠበት ጊዜ ድረስ ያለው የጀርባ ታሪክ በንጹሃን ደም የተጨማለቀ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ ።ይህ ግለሰብ ተስፋዬ መረሳ ይባላል ።ህወሃት ጫካ በነበረበት ጊዜ ተራው ታጋይ ከሴት ጋር የፍቅርም ሆነ የግብረ ስጋ ግኑኝነት ማድረግ እንደማይፈቀድለት አስገራሚው የፓርቲው ህግ ይደነግጋል ።ይህ ህግ እስከ 1981 አ.ም የቆየ ሲሆን የበላይ አመራሩ ግን የፈለገውን የማድረግ መብት ነበረው ።

በኢትዮጵያ የታሰሩት ሁለቱ ስዊድናውያን ጋዜጠኞች፤እንዲሁም ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ እና ሂሩት ክፍሌ ተፈቱ

ኢሳት ዜና:-ኢትዮጵያ ማርቲን ሽብዬ እና ጆሀን ፔርሰን  ለተባሉት ሁለቱ ዊድናውያን ጋዜጠኞች ይቅርታ ማድረጓን አንድ ከፍተኛ ባለስልጣን አስታወቁ። ከስዊድናውያኑ ጋዜጠኞች በተጨማሪ የ አውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ውብሸት ታዬ እና በነ ጋዜጠኛ ኤልያስ ክፍሌ መዝገብ የተከሰሰች  ሂሩት ክፍሌ በምህረት ተፈትተዋል። አሶሲየትድ ፕሬስ ባለስልጣኑን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ የተፈችዎቹ ይቅርታ የጸደቀው፤ በሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር በአቶ መለስ ዜናዊ ነው ።

Monday, September 10, 2012

እናንተ ወያኔዎች እንደ ቀትር እባብ መቅበዝበዛችሁን ትታችሁ እንደ ሰው አስቡ! ከፍቅሬ ዘለቀው



የአንባገነኖች ቁንጮና የዘረኞች መሀንድስ መለሰ ዜናዊ ሞት ነሐሴ 14፣ 2004 ዓ ም ይፋ ከተደረገ ጀምሮ የመንግሰቱ አቀንቃኞች፣ ደጋፊዎች፣ ሆድ አደሮች፣ ካድሬዎችና ሹማምንቶች ድንጋጤ ከመጠን ያለፈ ሆኖ እንደታየ ለመታዘብ በቅተናል። እውን ይህ ሁሉ ድንጋጤና መርበትበት እነሱ እንደሚሉት አገሩን የሚወድ፣ አርቆ አሳቢ፣ የልማት መሀንድስ፣ የአፍሪካ አባት፣ ኢየሱስ፣ ወዘተ… የሆነውን ንጉሳቸውን በማጣታቸው ነውን? መልሱ ግን አይደለም ነው። በሕዝብ አገልጋይነት ስም፣ በጌታቸው አጋፋሪነት የሕዝብን ንብረትና ሀብት በመዝረፍ ያገኙት የነበረው ጥቅም ሲቀር እየታያቸው እንጂ። 

Sunday, September 9, 2012

የኦጋዴን በህራዊ ነጻ አውጭ ግንባር ከመንግስት ጋር ድርድር ጀመረ

ኢሳት ዜና:-ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ በኬንያው ፕሬዚዳንት ምዋይ ኪባኪ አነሳሽነት በኢህአዴግ መራሹ መንግስትና በኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር መካከል እኤአ ከመስከረም 6 እስከ 7፣ 2012 ባሉት ቀናት ውስጥ ድርድር ተካሂዷል።

ውይይቱ የተመራው በኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር የውጭ ጉዳይ ሀላፊ በሆኑት አቶ አብዱራህማን ማሀዲ እና በመከላከያ ሚኒስትሩ ሀሰን ፈርጌሳ መካከል ነው።

በጄነራል ሳሞራ ዩኑስ የሚመሩ የህወሀት አባላት ጀነራሎች የመለስ ቦታ የሚገባው ለኛ ነው የሚል ጥያቄ ማንሳታቸው ተሰማ

ኢሳት ዜና:-ከኢህአዴግ  ሥራ አስፈፃሚ ሾልከው  የወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፤ ጀነራል ሳሞራ ዩኑስ እና በሥራቸው ያሉ የህወሀት ጀነራሎች ለጠቅላይ ሚኒስትርነት ብቁ የሆነ ሰው ከነሱ መካከል ስላለ በመለስ ቦታ ምንም ዓይነት ሹመት እንዳይሰጥ  መልዕክት አስተላልፈዋል።

ጀነራሎቹ፦“መለስን መተካት የሚችል ብቁ ሰው አለን። ከኛ ፈቃድና ዕውቅና ውጪ ማንም ጠቅላይ ሚኒስትር ሊሾም አይችልም!”ነው ያሉት።የጀነራሎቹ መልዕክትና አቋም መሰማቱን ተከትሎ በኢህአዴግ አመራሮችና አባላት መካከል ጭንቀት መፈጠሩም ታውቋል።

ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ለ17 ቀናት የሚቆይ ስልጠና ለዩኒቨርስቲ መምህራን ይሰጣል

ኢሳት ዜና:-የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ድንገተኛ ሞት ተከትሎ በስልጣን ሽኩቻ ውስጥ የሚገኘው ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ፣ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችንና የመንግስት ሰራተኞችን በመጋበዝ፣ ለግንባሩ ያላቸውን ተአማኒነት በይፋ እንዲያረጋገጡ የነደፈው ስትራቴጂ በዩኒቨርስቲ መምህራን ይጀመራል።