Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Saturday, August 18, 2012

ብአዴን እየታመሰ ነው

ኢሳት ዜና:- ነሀሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
የብአዴን አባል የሆኑ ታማኝ የኢሳት ምንጮች እንደገለጡት ሰሞኑን የብአዴን የኮር አባላት ለሁለተኛ ጊዜ በአቶ በረከት መሪነት በባህርዳር ከተማ ስብሰባ አድርገዋል።

የአማራ ክልል የወጣቶች ፕሬዚዳንት የሆነው ወጣት ዘመነ ካሴ ከአገር መውጣቱና ለኢሳት  ቃለምልልስ መስጠቱ፣  በክልሉ የተነሳው የሙስሊሞች እንቅስቃሴ ከአቶ መለስ ዜናዊ የጤንነት ሁኔታ ጋር ተደማምሮ በብአዴን የኮር አባላት ላይ ከፍተኛ ፍርሀት እና አለመረጋጋት መፍጠሩ የስብሰባው ዋነኛ የመነጋገሪያ አጀንዳዎች ነበሩ።

ልዑል ሙሉጌታ አስራተ ካሳ ተባረሩ

ኢሳት ዜና:- ነሀሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ከውጭ ጉዳይ ሰራተኞች በደረሰው መረጃ ልኡሉ በትናንትናው እለት በ2 የደህንነት ሰዎች ታጅበው ምርር ብለው እያለቀሱ ከለንደን ኢምባሴ ወጥተዋል።

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንትን ለመምረጥ ፍትጊያው ቀጥሎአል

ኢሳት ዜና:- ነሀሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ከምግብ መመረዝ ጋር ተያይዞ በከፍተኛ ሕመም ምክንያት ከኃላፊነታቸው ለመነሳት ከአንድ ዓመት በፊት የስራ መልቀቂያ ጥያቄ ያቀረቡት የኦህዴድ እና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት እንዲሁም የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ አለማየሁ አቶምሳ እስካሁን ጥያቄያቸው ምላሸ ባለማግኘቱ ፣ እርሳቸውን ማን ይተካ የሚለው ጥያቄ በኦህዴድ ውስጥ ከፍተኛ ውዝግብ መፍጠሩ ታውቋል።

በጳጉሜ ወር 2002 ዓ.ም በአዳማ በተካሄደው የኦህዴድ 6ኛ ድርጅታዊ ጉባዔ ተመርጠው የፓርቲውን የሊቀመንበርነት ሥልጣን ከአቶ አባዱላ ገመዳ የተረከቡት አቶ አለማየሁ ብዙም ሳይቆዩ በመስከረም ወር 2003 ዓ.ም የክልሉ ፕሬዚዳንት ሆነው ተሹመዋል፡፡

Friday, August 17, 2012

ጄነራል ሳሞራ የኑስ በጠና ታመው ትላንት ምሽት ኢትዮጵያን ለቀቁ

EMF news: የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ አይታወቅም። ጠቅላይ ሚንስትሩ ይዘውት የነበረውን የጠቅላይ ጦር አዝዥነትን ሚና በማን ኃላፊነት ላይ ሊወድቅ እንደሚችል ግልጽ አልነበረም። 

ይህንን ክፍተት ለመሙላት ከጠቅላይ ሚንስትሩ ቀጥሎ የጦር አዛዥነቱን ሚና ጄነራል ሳሞራ የኑስ ተክቶ ይሰራል፤ ተብሎ ግምት ሲሰጥ ቢቆይም…አሁን ግን ሳሞራ የኑስም በድንገተኛ ህመም ስራቸውን ያቆሙ መሆኑን ለማወቅ ችለናል። ይልቁንም በትላንትናው ምሽት ህመማቸው ስለጠና፤ ለህክምና ወደውጭ አገር ለቀው ወጥተዋል። 

የአቶ በረከት ስምዖን ሽሙጥ: ከፍቅሬ ዘለቀው፣ ኖርዎይ


በባራክ ኦባማ አስተዳደር ዘመን ለመጀመሪያ ጊዜ በደቪድ ካምፕ ዋሽንግቶን የዓለም ምግብ ዋስትናና ፖለቲካ ፈተናዎች በሚል ለተዘጋጀው የግንቦት 18፣ 2012 የቡድን ስምንት (G8- summit) የመሪዎች ጉባኤ አምባገነኑ መለስ ዜናዊ በአለቃቸው ተጋብዘው ለመሳተፍ ከውጪ ይጠብቋቸው የነበረውን የኢትዮጵያንን ቁጣ በጓሮ በር ሸሽተው በመግባት በስብሰባው ላይ ዲስኩር እያሰሙ እያሉ ነበር የመላውን ኢትዮጵያ ህዝብ ድምፅ ባነገበ ጀግናና አለኝታችን አበበ ገላው ቁጣ ቀልባቸው ተገፎ ከዕለቱ ጀምሮ ምናልባትም ለፍፃሜ ህልፈተ-ህይዎታቸው በሽታ ተዳርገው፣ ከአንድ ወር በሗላም በገረጣ ፊትና በከሳ ሰውነት በድጋሜ በሜክሲኮ ዋና ከተማ በኢንዱስትሪ በበለፀጉ አገሮች ስብሰባ ላይ ለመጨረሻ ጊዜ የታዩት።

Thursday, August 16, 2012

የአቡነ ጳውሎስ ዜና እረፍት የተደበላለቀ ስሜት ፈጥረ

ኢሳት ዜና:-ነሀሴ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጻውሎስ ፓትሪያሪክ ርዕሰ ሊቀጻጻስት ዘኢትዮጵያ ሊቀጻጻሳት ዘአክሱም ወጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፣የዓለም አብያተክርስቲያናት ፕሬዚዳንት በ76 ዓመታቸው አርፈዋል።

20ኛ ዓመት የሲመት በዓላቸውን ሐምሌ 5 ቀን 2004 ዓ.ም በሸራተን ሆቴል ያከበሩት አቡነ ጻውሎስ በባልቻ ሆስፒታል በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ትላንት ለሊት አርፈዋል።

ኢትዮጵያውያን በተለይ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በጳጳሱ ዜና እረፍት የተደበላለቀ ስሜት ተስምቷቸዋል። የአዲስ አበባ እና የክልል ከተሞች ዘጋቢዎቻችን እንዳሉት ህዝቡ በዜና እረፍታቸው ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ሲነጋገር ውሎአል።

አቶ መለስ ዜናዊን ለመተካት አዲስ ህግ ተረቀቀ

ኢሳት ዜና:- ነሀሴ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን ለኢሳት እንደገለጡት ፍትህ ሚኒስቴር እጅግ ጥብቅ በሆነ ሚስጢር አዲስ ህግ አርቅቆ ለፓርላው የህግ ክፍል ልኳል። በከፍተኛ ሚስጢር በተያዘው በዚህ ህግ የማርቀቅ ስራ ላይ የተሻለ የህግ እውቀት አላቸው የተባሉ ሰዎች  ተሳትፈዋል።

አቶ መለስን የመተካቱ ነገር ያለቀለት ጉዳይ መሆኑን ባለስልጣኑ ገልጠዋል። ፓርላመው ምናልባትም የፊታችን ማክሰኞ ካልሆነም በሚቀጥለው ሳምንት ውስጥ በአንደኛው ቀን ከእረፍት ለአስቸኳይ ስብሰባ ተጠርቶ ረቂቅ ህጉን ያጸድቀዋል።

በደቡብ ክልል ከፖሊስ መጋዘን የጦር መሳሪያ ተዘረፈ

ኢሳት ዜና:- ነሀሴ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
በደቡብ ክልል ከሚገኘው ደራሼ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት መጋዘን ውስጥ  የጦር መሳሪያ መዘረፉ ተገለፀ፡፡የጦር መሳሪያው በጊዜያዊነት በመጋዘን ተሰብስቦ የነበረው በአሁን ወቅት በ“አሌ” ወረዳ የሚገኘው ህዝብ፤ በደራሼ ልዩ ወረዳ ስር በነበረበት ወቅት ነው።

በ1997 ዓ.ም የወረዳ ህዝብ ላቀረበው ራስን ችሎ የመዋቀር ጥያቄ አመራሩ ተግባራዊ ምላሽ እንደሚሰጥ  ቃል ቢገባም፤ በወቅቱ በነበረው አገር አቀፍ ምርጫ  በአካባቢው ቅንጅት ማሸነፉን ተከትሎ ቃል የተገባው ሳይተገበር በመቅረቱ፤በህዝቡ ዘንድ ቅሬታ ተፈጥሮ መቆየቱን የፍኖተ-ነፃነት ዘገባ ያስረዳል።

ሰበር ዜና: ቅዱስ ፓትርያርኩ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

(ደጀ ሰላም ነሐሴ 10/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 16/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ ኻያኛ ዓመት በዓለ ሢመታቸውን ከሐምሌ 5 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ወሩ መገባዳጃ ሲያከበሩ የቆዩት አምስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በጠና ታመው ነሐሴ 8 ማምሻውን ወደ ደጃዝማች ባልቻ ሆስፒታል ከገቡ በኋላ በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ማረፋቸውን ምንጮቻችን እየገለጹ ነው።

Wednesday, August 15, 2012

አቶ ስብሐት ነጋ ስለ አቶ መለስ ዜናዊ በ10 ቀናት ውስጥ መመለስ መናገራቸው ስህተት እንደነበረ ለኢሳት ገለጡ

ኢሳት ዜና:- ነሀሴ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
አቶ መለስ ዜናዊ በ10 ቀናት ውስጥ ወደ ስራ ገበታቸው እንደሚመለሱ ከሶስት ሳምንት በፊት ያስታወቁት አቶ ስብሐት ነጋ አባባላቸው ስህተት መሆኑን ለኢሳት ገለጡ።

አቶ በረከት ስምኦን ከአዲሱ አመት በፊት አቶ መለስ ወደ ስራ ገበታቸው እንደሚመለሱ የሰጡትን መግለጫ በተመለከተ ይህንን የማረጋገጥም ሆነ የማስተባበል መረጃ እንደሌላቸው አመልክተዋል።

ኢነጋማ በፍትህ ጋዜጣ ላይ የተወሰደውን እርምጃ በጥብቅ አወገዘ

ኢሳት ዜና:-” ነሀሴ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
የወቅቱ የኢትዮጵያ አስተዳደር የፍትህ ጋዜጣን  ማገዱ፤ በኢትዮጵያ ጭል ጭል ሲል የነበረው የፕሬስ ነፃነት ሙሉ ለሙሉ መዳፈኑን የሚያመለክት ነው” ሰል  ኢነጋማ ገለጸ።

በስደት የሚገኘው የ ኢትዮጵያ ነፃ ጋዜጠኞች ማህበር፦“በፍትህ ጋዜጣና በአዘጋጁ ላይ እየተወሰደ  ያለው እርምጃ፤ በኢትዮጵያ የፕሬስ ነፃነት መብት ጨርሶ መጥፋቱን የሚያረጋግጥ ክስተት ነው” በሚል ርዕስ ባወጣው መግለጫ፤ፍትህ ጋዜጣ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ በኢትዮጵያ ብቸኛ የነፃ ፕሬስ አማራጭ በመሆን፤ የህዝብን የማወቅ መብት ተግባራዊ ለማድረግ የተጣለባትን ተጽ እኖና አፈና ተቋቁማ  ስትንቀሳቀስ  መቆየቷን አውስቷል።

ኢራፓ፦”አገሪቷን ማን እንደሚመራት ባለመታወቁ በስጋት እየታመሰች ትገኛለች”አለ

ኢሳት ዜና:-ነሀሴ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሥራ ላይ አለመሆናቸው ከተነገረና ከተረጋገጠ ጊዜ አንስቶ፣ ኢትዮጵያን ማን እየመራት እንደሆነ ለሕዝብ ይፋ ባለመገለጹ አገሪቱ በወሬ፣ በሐሜት፣ በፍርኀትና በሥጋት እየታመሰች ትገኛለች ሲል የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ ገለጸ።

ኢራፓ ባወጣው ወቅታዊ መግለጫ   አገሪቱ በማን እየተመራች እንደሆነ  ለኢትዮጵያ ህዝብ በግልጽ እንዲነገረው አሣስቧል።
ኢሳት ዜና:- ነሀሴ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
 “ጠቅላይ ሚ/ር መለስ ዜናዊ ዞር ሲሉ፤ ግብፆች ፦” ኢትዮጵያውያን ከጥቅማቸው በተቃራኒ ይቆማሉ” ብለው ማሰባቸው ስህተት ነው” ሲሉ አንድ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለስልጣን ተናገሩ፡፡

በኢፌድሪ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር የኮሙኒኬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ረዳ ይህን ያሉት፤ አንድ የግብጽ የመስኖ ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለስልጣን የዛሬ ሳምንት ፦” ከመለስ ዜናዊ በሁዋላ የሚኖረው አዲሱ የኢትኦጵያ አመራር -ከአዲሶቹ ከግብጽ መሪዎች ጋር በጋራ  በመሆን  በዓባይ ወንዝ ምክንያት  በአገሮቹ መካከል የተፈጠረውን ውጥረት ያረግቡታል የሚል እምነት አለኝ” ማለታቸውን ተከትሎ ነው።

አስቸኳይ የምግብ እርዳታ የሚፈልጉ ሰዎች ቁጥር 16 በመቶ ጨመረ

ኢሳት ዜና:- ነሀሴ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ግብርና ሚኒስቴር እና የውጭ ለጋሾች ትናንት በጋራ ያቀረቡት ሰነድ እንደሚያሳየው ከሀምሌ እስከ ታህሳስ ወር ባለው ጊዜ ውስጥ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ የሚፈልጉ ዜጎች ቁጥር ከ3 ሚሊዮን 200 ሺ ወደ 3 ሚሊዮን 700 ሺ ከፍ ብሎአል። ለእነዚህ ተረጅዎች ከ189 ሚሊዮን ዶላር ወይም ከ3 ቢሊዮን 4 መቶ ሚሊዮን በላይ ብር እንደሚያስፈልግ ታውቛል።

41 በመቶ የሚሆኑት ተረጅዎች በሶማሊ፣ 27 በመቶ በኦሮሚያ፣ 10 በመቶ በትግራይ፣ 8 በመቶ በአማራና በደቡብ፣ እንዲሁም 4 በመቶ በአፋር ክልል ይገኛሉ። በአጠቃላይ 193 ሺ 866 ሜትሪክ ቶን ምግብ እንደሚያስፈልግ በሰነዱ ተመልክቷል።

Tuesday, August 14, 2012

የአዜብ መስፍን እህት ሰርግ ተሰረዘ

የኢሳት ዜና የጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ቤተሰቦች ለመስከረም 10 ታቅዶ የነበረ ሰርግ እንዲሰረዝ ማድረጋቸውን ታማኝ የኢሳት ምንጮች ጠቁመዋል።

ከጠቅላ  ሚኒስትሩ ደብዛ መጥፋት ጋር በተያያዘ በቤተመንግስት አከባቢ በተፈጠረው ቀውስና ትርምስ የተጨነቁት እነዚሁ የቤተሰብ አባላት የወ/ሮ አዜብ ታናሽ እህት ሶሻል ይልማ ሰርግ ለመሰረዝ መገደዳቸውን  ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የኢሳት ምንጮት ጠቁመዋል።

ሰራዊቱ አሁንም በአንደኛ ደረጃ ተጠንቀቅ ላይ ነው

የኢሳት ዜና: የአቶ መለስ ዜናዊን መሰወር ተከትሎ በኢትዮጵያ ያለው ውጥረት እንደቀጠለ ሲሆን፤ ጦር ሰራዊቱ በአንደኛ ደረጃ ተጠንቀቅ እንዲቆም የታዘዘው፤ በቅርቡ በተመሰረተውና በጦር ሰራዊቱ ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ ውይይት በጫረው ነጻ የኢትዮጵያ ሰራዊት ንቅናቄ (ነኢሰን) መግለጫ ጭምርም እንደሆነ አስተማማኝ የውስጥ ምንጭ ገለጸ።

ለመከላከያ ሚኒስቴር ቅርበት ያላቸው ምንጮቻችን እንደገለጹት፤ በኢትዮጵያ በቅርቡ የተመሰረተበትን መግለጫ የበተነው ነጻ የኢትዮጵያ ሰራዊት ንቅናቄ፤ ከተመሰረተ ግዜ ጀምሮ በኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት ውስጥ ከፍተኛ ውይይት እንደጫረና፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አለመኖር ታክሎበት ስጋት በመፍጠሩ ምክንያት፤ አየር ሀይሉን ጨምሮ የጦር ሰራዊቱ በሙሉ በአንደኛ ደረጃ በተጠንቀቅ እንዲቆም መደረጉ ታውቋል።

(Breaking News) Abune Paulos hospitalized ፓትርያርኩ በጠና ታመዋል


. ማምሻውን ወደ ባልቻ ሆስፒታል ገብተዋል

(Deje Selam, August 14/2012):- Patriarch of the Ethiopian Orthodox Tehwadeo Church, His Holiness Abune Paulos, is hospitalized today at Balcha Hospital.  Sources close to the Patriarchate say "he is in critical condition". The patriarch has been attending medications for a long time. Detail news coming soon. Stay tuned.

(ደጀ ሰላም፤ ነሐሴ 8/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 14/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ ኻያኛ ዓመት በዓለ ሢመታቸውን ከሐምሌ 5 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ወሩ መገባዳጃ ሲያከበሩ የቆዩት አምስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በጠና ታመው ምሽቱን ወደ ደጃዝማች ባልቻ ሆስፒታል መግባታቸው ተሰማ፡፡

አቦይ ስብሐት “አዲስ አድማስ ጋዜጣ ውሸቱን ነው መለስ በቤታቸው የሉም” አሉ


ስለ አቶ መለስ ዜናዊ ማውራት ደክሞኝ ነበር። ሳስበው ሳስበው እርሳቸው የሆኑትን ሆነው ደከመኝ ሳይሉ እኔ እንዴት ደከመኝ እላለሁ ብዬ ተፀፅቻለሁ። መቅደላዊት የተባለች ወዳጄም ከሪያድ በሰደደችልኝ አስተያየት ሀዘኑን እንረሳው ዘንድ ስለርሳቸው መጨዋወታችንን እንቀጥል እንጂ ድንኳን ሳይነሳ የምን ዝም ዝም ነው የሚል ወቀሳ ሰንዝራልኛለች። እኔም በሆዴ የምን ሀዘን ብዬ ሳበቃ  “እውነት ግን ምን ነካኝ…!” ብዬ ሂሴን ውጫለሁ!

ስደት መርረረን......ከጌዲዮን ደሳለኝ\ኖርዌይ\

ከጌዲዮን ደሳለኝ\ኖርዌይ\
ተሰደን ተሰደን አላልቅ ስላልን እንጂ በጣም ተሰደናል እኮ፥ አገራችንን ለቀን እየወጣን ለባዳ ሳናቀው እያስረከብን እኮ ነው፥፥
የድሮው የማናቀው የቅኝ ግዛት ታሪክ ተከረባብቶ ወደ ወደተስፋይቱ ምድር ወደ አገሬ ኢትዮጵያ ከች እያለ ነው፥፥ እርግጥ ነው አንዳንዴም የመለስ ስርአት ሲመረን አንዳንዴም የነጮቹ ኑሮ ሲያስቀናን መጀመርያ ትዝ የሚለን ስደት ነው፥፥ 
አሁን አሁን ግን የምንሰደደው የሆነ ከአቅም በላይ ፍለፊታችን ግትር ያለ የሰይጣን ተራራ የሚሉት አይነት ባላንጣ የቆመ መሰለኝ፥፥ እኛም ደሞ ተልፈስፍሰናል፥ ምን እንደምንፈልግ እንኩአን ያወቅነው አልመሰለኝም፥፥ ሰይጣኑን በማስወጣት ፈንታ ለሰይጣኑ መገበር ጀምረናል፥፥