Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Saturday, July 28, 2012

ዘረኛውና አምባገነኑ መለስ ዜናዊ አሁንም ከማገገሚያ ክፍል እንዳልወጣ ምንጮች ገለጹ

 ግንቦት ሰባት ዜና፣, Source: www.ecadforum.com
ቤልጂዬም ብራስል በሚገኘው የሴይንት ሉክ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ውስጥ ህይወታቸው አደጋ ላይ የወደቁ ሰዎች የመተንፈሻና የፈሳሽ ምግብ ቱቦዎ ተገጥሞላቸው በሚተኙበት የሪከቨሪ ሩም እየተባለ በሚጠራው የህክምና ክፍል ውስጥ እንደሚገኝ ከሆስፒታል ምንጮች ያገኘነው መረጃ አረጋገጠ።

መለስ ዜናዊ እራሱን ስቶ በቻርተር አውሮፕላን ወደ ቤልጂዬም ከተላከ ወዲህ ላለፉት 3 ሳምንታት እራሱን መቆጣጠር በማይችልበት ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ የገለጹ ምንጮች ከአሁን አሁን ይሞታል ተብሎ ሲጠበቅ ነፍሱ መለስ እንደሚልና ተሽሎታል ተብሎ ሲታሰብ ደግሞ ወዲያውኑ መልሶ እንደሚወስደው አረጋግጠዋል።

የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶክተር ቴዎድሮስ አድሀኖም፤ በአቡነ ጳውሎስ ተሾሙ።

ኢሳት ዜና:- ሐምሌ ፳ (ሀያ)ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
 የአቡነ ጳውሎስ 20ኛ ዓመት በዓለ-ሲመት ሐምሌ 16 ቀን 2004 ዓ.ም ምሽት በሼራተን አዲስ ለሁለተኛ ጊዜ  በተከበረበት ጊዜ  ይፋ የሆነውንና በፓትርያርኩ ስም በ 200 ሚሊዮን ብር ወጪ ሊገነባ የታሰበውን ሆስፒታል በበላይነት እየተቆጣጠሩ እንዲያስፈፅሙ  ነው ሚኒስትር ቴዎድሮስ የተሾሙት።

በዚሁ በሸራተን በተካሄደው የፓትርያርኩ  በዓለ-ሲመት ዝግጅት ላይ፤ የክብር እንግዳ የነበሩትን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩን አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝን እና  ዶክተር ቴዎድሮስ አድሀኖምን ጨምሮ በርካታ የመንግስት ባለስልጣናት ታድመዋል።

ሞያሌ ኣካባቢ በተነሳው ግጭት ከ20 በላይ ሰዎች ተገደሉ::

ኢሳት ዜና:- ሐምሌ ፳ (ሀያ)ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት የሞያሌ ነዋሪዎችን በስልክ አነጋግሮ ባጠናከረው መረጃ ከሶስት ቀናት በፊት በተነሳው ተቃውሞ ከ20 በላይ ሲቪሎችና 1 የፌደራል ፖሊስ ተገድለዋል። 

7 ፖሊሶች ደግሞ በጽኑ ቆስለዋል። ግጭቱ የሶማሊ ብሄረሰብ ተወላጅ በሆኑ ገሪዎችና የኦሮሞ ተወላጅ በሆኑ ቦረናዎች መካከል የተፈጠረ ቢሆንም፣ የሁለቱም ክልል ፖሊሶች ጎራ ለይተው መታኮሳቸውን ነው ነዋሪዎች የሚገልጡት።

Wednesday, July 25, 2012

በመልጋ ወረዳ በተነሳ ግጭት ከ19 በላይ ፖሊሶች በጽኑ ቆሰሉ

ኢሳት ዜና:-ሐምሌ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
በትናንትናው እለት ከአዋሳ ከተማ  በ26 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘዋ ማልጋ ወረዳ  በተፈጠረው ግጭት 3 የፌደራል ፖሊስ አባላት በጽኑ መቁሰላቸውን የዘገብን ቢሆንም፣ ዛሬ ዘጋቢያችን ተዘዋውሮ ያጠናከረው መረጃ እንደሚያመለክተው ከ19 በላይ ፖሊሶች እና ከ20 በላይ ነዋሪዎች በጽኑ ቆስለዋል።

አናታቸው የተፈነከተ ፣ እግራቸው የተሰበረ፣ እንዲሁም በጥይት የቆሰሉ የፌደራል ፖሊስ አባላት መንገድ ላይ ወድቀው ይታዩ ነበር። በገበያ ላይ የነበረው የአካባቢው ህዝብ ባገኘው መሳሪያ ሁሉ በመጠቀም ከፖሊሶች ጋር ግብ ግብ የገጠመ ሲሆን፣ መሳሪያ የታጠቁ ነዋሪዎች፣ አፈሙዛቸውን ወደ ፖሊሶች በማዞር በርካቶችን አቁስለዋል።

የአባ ጳውሎስ ዘመነ ፕርትርክና 20ኛ ዓመት በዓለ ሢመት በሼራተን አዲስ ተከበረ

ኢሳት ዜና:- ሐምሌ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ደጀ-ሰላም እንደዘገበው፤የፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት እና ራእይ ለትውልድ ፤  በእንግሊዝኛው አጠራር ፦ /Vision for Generation/ የተባለው አካል የጥቅም ትስስር የፈጠሩበት የሼራተኑ በዓለ ሢመት ዝግጅት የተከናወነው፤ በቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ይኹን አለያም በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጽ/ቤት፤ እስካሁን  አልታወቀም።

በዚሁ  የአቡነ ጳውሎስ  20ኛ ዓመት  በዓለ-ሢመት ላይ፤ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የአብያተ እምነት መሪዎችን፣ አምባሳደሮችንና ታዋቂ ግለሰቦችን ጨምሮ  በሺህ የሚቆጠሩ እንግዶች መታደማቸው ታውቋል። ይህ ደማቅ  ዝግጅት ከጥቅም ትስስር ባሻገር÷ በግንቦቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ እና ውሳኔዎች ክፉኛ የተጋለጠውን የአባ ጳውሎስን ማንነት ለማደስ የታሰበበት ‹የሕዝብ ግንኙነት› ሥራ ነውም ተብሏል።

የድህረ መለስ ዜናዊ ኢህአዴግ ምን መልክ ይኖረው ይሆን?

መለስ ብቻቸውን ኢህአዴግ ናቸው!

የኢህአዴግ መስራች ከሆኑት ፓርቲዎች የበላይ የሆነው ህወሓት በተለይም በጣምራ አመራር (collective leadership) ይታወቅ ነበር፡፡ ከ1971 ዓ.ም በፊት ሁለት ደረጃዎች ለነበሩት የህወሓት አመራር ሁለተኛው ረድፍ ላይ ተቀምጠው የነበሩት መለስ ዜናዊ በዓመቱ በተካሄደው የድርጅቱ ኮንግረስ ወደ መጀመሪያው ረድፍ አመራር መጡ፡፡ 

ከዚያ ቀደም የመጀመሪ ረድፍ የነበሩት አባይ ፀሐዬ፣ ስብሃት ነጋ፣ አረጋዊ በርሄ፣ ግደይ ዘርዓ ፅዮንና ስዩም መስፍን ነበሩ፡፡ መለስ ዜናዊ ወደነኚህ የመጀመሪያ ደረጃ አመራር የመጡበት ምክንያት በወቅቱ ኮንፍረንስ የተወሰነው ሶሻሊስት ፓርቲ የመመስረት ዕቅድ ነበር፡፡ ማዕከላዊ ኮሚቴው ይህን የሶሻሊስት ፓርቲ እንዲመሩ የሰየማቸው አቶ መለስ ዜናዊ ውሳኔው የጦር ሜዳ ውሎ ቀንሶላቸዋል፡፡ ቀጥሎም የካድሬ ት/ቤት ዋነኛ ተዋናይ፣ አንባቢና የሀሳብ አመንጪ ሆኑ፡፡

Tuesday, July 24, 2012

እነ ናትናኤል መኮንን ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ተዛወሩ

                            -አቶ ዘሪሁን ገ/እግዚአብሔር ለብቻቸው ታሰሩ
በእነ አንዱዓለም አራጌ የክስ መዝገብ ተከሰው በቅርቡ የተፈረደባቸው የአንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ም/ ቤት አባል መምህር ናትናኤል መኮንን፣ የቀድሞ የፓርላማ አባል አቶ አንዱዓለም አያሌው የአንድነት ፓርቲ የባህር ዳር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሻምበል የሺዋስ ይሁንዓለም፣ አቶ ክንፈሚካኤል ደበበ/አበበ ቀስቶ/ ፣ አቶ ዮሐንስ ተረፈና አቶ ምትኩ ዳምጤ ከነበሩበት ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ከፍተኛ ጥበቃ ወዳለበት ቂሊንጦ ወደሚገኘው እስር ቤት መዛወራቸውን ቤተሰቦቻቸው ለዝግጅት ክፍላችን
ገልፀዋል፡፡ 

Ethiopia and Eritrea: Rising Tensions Amid New Opportunities for Engagement

By Jason Mosley, Associate Fellow, Africa Programme, Maleda Times
The latest report from the United Nations Monitoring Group on Somalia and Eritrea has stirred tensions between Eritrea, Ethiopia and Somalia.

Eritrea has seized on a selective reading of the report to call for the lifting of UN imposed sanctions, a call already rebuffed by the Monitoring Group’s Coordinator. The diplomatic fallout is likely to continue as Ethiopia and its allies push for continued (or tightened) sanctions on Eritrea.

የድምጻችን ይሰማ አመራሮች ዛሬ ፍርድ ቤት ቢቀርቡም፣ ከበር መመለሳቸው ተሰማ

ኢሳት ዜና:- ሐምሌ ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ባለፈው አርብ 70 የሚሆኑ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ፍርድ ቤት ቀርበው 28 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸዋል። በዛሬው እለት ደግሞ 8 የአመራር አባላት አራዳ ምድብ ችሎት ቢቀርቡም ወዲያውኑ ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደርጓል።

የመንግስት ታጣቂ ሀይሎች ድምጻችን ይሰማ በማለት ጥያቄ ባቀረቡ ሙስሊሞች ላይ የጅምላ እስር እና ድብደባዎችን ፈጽመዋል።  ትናንት እሁድና ዛሬ ሰኞ የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት ብቻ በአንዋር መስጊድ አካባቢ ሲዞሩ የታዩ ሲሆን፣ የፌደራል ፖሊስ ልዩ ግብረሀይል ፣ ጊዚያዊ ጣቢያ ብለው ባቋቋሙት ኡመር ሰመተር የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ በሜጋ አምፊ ቲያትር እና በአዲስ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ሰፍረው እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሎአል።

የመልጋ ወረዳ ህዝብ ከ ፌደራል ፖሊስ አባላት ጋር ሲጋጭ ዋለ

ኢሳት ዜና:- ሐምሌ ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ከአዋሳ ከተማ  በ26 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘዋ ማልጋ ወረዳ ዛሬ በተፈጠረው ግጭት 3 የፌደራል ፖሊስ አባላት በጽኑ ሲቆስሉ ከህዝቡም በተመሳሳይ ሰዎች ቆስለዋል።

 የአካባቢው ነዋሪዎች ለእረፍት ወደ አካባቢው ከሄዱ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ጋር በመሆን፣ በቅርቡ በሲዳማ ዞን የተከሰተውን ችግር እየተወያዩ በነበረት ጊዜ የፌደራል ፖሊስ አባላት  ለመበትን ጥረት በማድረጋቸው ግጭቱ መከሰቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጠዋል ”

Sunday, July 22, 2012

መድረክ-ወደ-ግንባር-ተሸጋገረ

ሐምሌ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፣ የኦሮሞ ህዝቦች ኮንግረስ /ኦህኮ / ፣ የኦሮሞ ፌደራሊስት ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ኦፌዴን / ፣ አረና ትግራይ ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ህብረት ፣ የኢትዮጵያ ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ /ኢሶዴፓ/ ናቸው ዛሬ በጋራ ግንባር የመሰረቱት።

አቶ ጥላሁን እንዳሻው ሊቀመንበርነት ፥ ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳን ምክትል ሊቀመንበርና የፋይናንስ ጉዳይ ሀላፊ ፣ ዶክተር መረራ ጉዲናን ምክትል ሊቀመንበርና የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ ፣ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስን ምክትል ሊቀመንበርና የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፣ አቶ ገብሩ አስራትን ምክትል ሊቀመንበርና የውጭ ጉዳይ ኃላፊ እንዲሁም ዶክተር ሞጋ ፍሪሳን ዋና ፀኃፊ አድርጎ ግንባሩ መርጧል።